ኑ እና ጐንደርን እናልማ

እናንተም አድጋችሁ ሀገርን ጥቀሙ
የነገስታት ሃገር የመናገሻ ከተማ ጎንደር እንኳን ደህና መጣችሁ የኢንዱስትሪ እና ኢንቨስትመንት መምሪያ ከእርስዎ ጋር በጋራ በመስራታችን ኩራት ይሰማናል! ያግኙን የአፍሪካ መናገሻ
የቱሪስት መስዕህብ፤ ብዙ አማራጮች ያላት!
አገልግሎቶች

ለምን ጎንደር?

ጎንደር ከተማ የቱሪስት መስዕህብ ያሉባት ከተማ መሆና ጋር ተያያዞ ጥሩ የገበያ ዕድል ያላት ከተማ መሆና፣ የተሻለ የመሰረተ ልማት  ማለትም የየብስ እና የአየር ትራንስፖርት፣ የውሃ አቅርቦት፣ የደረቅ ወደብ ተጠቃሚነት ፤ የተማረ የሰው ሃብት እና ሌሎችም መልካም አጋጣሚዎች ያሉ በመሆኑ ጎንደርን ለኢንቨስትመንት ተመራጭ ያደርጋታል፡፡ 

በአሁኑ ወቅት ከተማችንን ብሎም ክልላችንን በፍጥነት ለማልመትና ለማሳደግ፣ የስራ አጥ ቁጥርን ለመቀነስና ድህነትን  ለመቅረፍ የኢንዱስትሪው ክፍለ ኢኮኖሚ የመሪነቱን ሚና ይጫወታል፡፡ ስለሆነም መንግስት አምራች ኢንዱስትሪዎችን ልዩ ትኩረት በመስጠት ከተማችንን ሆነ ክልላችንን ወደ ተሻለ ደረጃ ለማሳደግ በርብርብ ላይ ይገኛል፡፡ በሃገራችን ለረጅም ጊዜ ተንሰራፍቶ የቆየዉን ስር የሰደደ ድህነትን በማስወገድ በምትኩ ለዜጎቻችን የተሻለ የገቢ ምንጮችን በመፍጠር የኑሮ ደረጃቸዉን በማሻሻል በአለም ላይ ከሚገኙ መካከለኛ ገቢ ካላቸዉ የአለም አገራት ተርታ ለማሰለፍና በከተሞች ድህነትን ለመቀነስና የነዋሪዉን የኑሮ ሁኔታ ለማሻሻል በዋናነት ከተዘረጉት ስትራቴጂዎች ዉስጥ የኢንዱስትሪው ክፍለ ኢኮኖሚ የመጀመሪያዉን ስፍራ እንደሚይዝ ይታወቃል፡፡

 የጎንደር ከተማ አስተዳደር በ2022 ዓ/ም በአምራች ኢንዱስትሪና በቱሪዝም በኢትዮጵያ ቀዳሚ ተወዳዳሪና ተመራጭየኢንቨስትመንት መዳረሻ ሆኖ ማየት ነው፡፡

  • በአገር አቀፍ፣ ክልላዊና ከተማ አስተዳደራዊ ሁኔታዎች እና አዝማሚያዎች ጋር በማጣጣም የዘርፉን ማነቆዎች በመለየት እና የመፍትሄ አቅጣጫዎችን በማመላከት በክልሉ ለግሉ ክፍለ ኢኮኖሚ ሳቢ እና ምቹ ሁኔታዎች እንዲፈጠሩ ማድረግ፤
  • አገር አቀፍ፤ ክልላዊና ከተማ አስተዳደራዊ ተሞክሮዎች ላይ ተመስርቶ የኢንቨስትመንት አማራጮችን በማስፋትና ለባለሃብቱ ወሳኝ የሆኑ መረጃዎችን በማደራጀት፣ አስቀድሞ በመዘጋጀት፣ ውጤታማ የፕሮሞሽን ሥራ በማከናወን የኢንቨስትመንት ፍሰትን ማሳደግ፤
  • የከተማ አስተዳደሩን ኢንዱስትሪና ኢንቨስትመንት አገልግሎት አሰጣጥን ተገልጋይ ተኮር በማድረግ፣ የአገልጋዩን አቅም በመገንባትና በቴክኖሎጂ በመደገፍ ዓለም አቀፍ ደረጃውን የጠበቅ የአንድ ማዕከል አገልግሎት በመስጠት የኢንቨስትመንት ውጤታማነትን እና ዘላቂነትን በማረጋገጥ የከተማውን ኢኮኖሚ መዋቅራዊ ሽግግር ማፋጠን፤
  • ገቢ ምርቶችን በሀገር ውስጥ በማምረት የሚተኩ ማኑፋክቸሪንግ እና ሌሎች አምራች ኢንዱስትሪዎችን በክልሉ ማስፋፋት፤
  • ለውጭ ገበያ የሚቀርቡ ምርቶችን የሚያመርቱ የማኑፋክቸሪንግ፣ የግብርና እና ሌሎች አምራች ኢንዱስትሪዎችን ማስፋፋትና ተወዳዳሪነታቸውን ማጎልበት፤
  • በቱሪዝምና በሌሎች አስቻይ የአገልግሎት ዘርፎች የግሉ ኢንቨስትመንት እንዲስፋፋ እና ተጠናክሮ ለኢኮኖሚው ጉልህ አስተዋጽኦ የሚያደርግበትን ሁኔታ ማመቻቸት፤
  • በኢንቨስትመንት የተሰማሩ የግል ባለሀብቶችን ደግፎ ውጤታማ በማድረግ ኢንቨስትመንትታቸውን እንዲያስፋፉ፣ እንዲያስተሳስሩ እና ጥራት ያለው የስራ እድል እንዲፈጥሩ የሚያስችሉ ድጋፎችን ማድረግ፤

  • የላቀ አገልግሎት፤
  • ዘመናዊነት፤
  • የተገልጋይ ርካታ፤ ዝግጁነት፤
  • ቅንጅታዊ አሰራር፤

ዜናዎች

አገልግሎቶች

የኢንቨስትመንት ፍቃድ መስጠት

የኢንቨስትመንት ማስፋፊያና እድሳት

የኢንቨስተመንት ፈቃድ ምትክ፣ ለውጥ፣ ዝውውርና ማስተላለፍ

የኢንቨስትመንት ፍቃድ ስረዛ

አሃዞች

1
ኢንዱስትሪ ፓርክ
0
ኢንቨስተር
0
ፕሮጀክቶች
0
የስራ ዕድሎች

የጎንደር ከተማ አጠቃላይ ገጽታ

ምቹ ሁኔታዎች

የመሬት አቅርቦት

ለማንፋክቸሪንግ አና በአግሮ ፕሮሰሲንግ ለሚሰማራ ባለሀብት ቦታ በምደባና በዝቅተኛ የሊዝ ዋጋ ይሰጣል፣ ለሆቴሎችና ሌሎች ዘርፎች በጫራታ እየተሰጠ ያለበት ከተማ ነው ጎንደር፡፡

መሰረተ ልማት

በከተማችንም ሆነ በኢንዱስትሪ መንደር በተሻለ መልኩ የተሟላ መሰረተ ልማት አለ ማለት ይቻላል (ከመንገድ ፣ ፣ከውሃ አቅርቦት ፣ የአየር እና የየብስ ትራንስፖርት፣ ደረቅ ወደብ ተጠቃሚነት የመሳሰሉት አገልግሎቶች ስኬታማ ናቸው በከተማችን፡፡

የሰው ሃይል

በከተማችን ሰፊ እና የተማረ የሰው ሀይል በመኖሩ በተመጣጣኝ ክፍያ በቂ ሰራተኛ ማግኘት የሚቻልበት ከተማነው ጎንደር ፡፡

ማበረታቻዎች

በከተማችን ባሉየፋይናንስ ተቋማት አማካኝነት ባለሀብቱ ብደር እያገኘ ነው፡፡ በተለይ ልማት ባንክ አፈጻፀሙ እንዲፀነክር ጥረት የሚያስፈልገው ቢሆንም ሁለት ዓይነት የብድር አቅርቦት እየሰጠ ነው፡፡

የኢንዱስትሪ ግብዓቶች

በአካባቢው ለኢንዱስትሪው ግባት ሊሆን የሚችል የእንስሳትና የሰብል ውጤቶች በሰፊው መገኘቱ /ሰሊጥ፣ ጥጥ፣የመሳሰሉት/

የገበያ ትስስር

በቅርብ እረቀት ባሉት ከሱዳን ጋር 220ኪ/ሜ፣ ከኤርትራ በ255ኬ/ሜ የደረቅ ወደብ የገበያ ትስስር ማድረግ መቻሉ፡፡የቱሪስት መስዕህብ ያሉባት ከተማ ከመሆኗ ጋር ተያይዞ ጥሩ የገበያ ዕድል ያላት ከተማ መሆኗ ሌሎችም መልካም አጋጣሚወች ያሉ በመሆኑ ጎንደርን ተመራጭ ከተማ ያደርጋታል ፡፡

የኢንቨስትመንት አማራጮች በማኑፋክቸሪንግ ፤ ማህበራዊ እና አገልግሎት ዘርፎች

የአግሮ ፕሮሰሲንግ ምግብ እና ፋርማሲቲካል

ቆዳና ጨርቃ ጨርቅ

ትምህርትና ጤና

ኮንስትራክሽን ግብዓትና ኬሚካል

ሆቴልና ቱሪዝም

የእንጨትና ብረታ ብረት

ቅይጥ ንግድ

አጋር አካላት

አድራሻ