ሰለ እኛ

በጎንደር ከተማ አስተዳደር ካሉት የክልሉም ሆነ የሀገሪቱ ከተሞች በተሻለ ሁኔታ ገና ያልተነኩ የኢንቨስትመንት አማራጮችና ምቹ ሁኔታዎች አሉት፣ እነኝህን ሀብቶችና የኢንቨስትመንት አማራጮች ወይም ፀጋዋችን ለቅሞ እና ለይቶ በመያዝ ለአልሚ  ባለሀብቱ በማስተዋወቅና ባለሃብቶችን በመሳብ ለአካበባው ህብረተሰብ የስራ ዕድል ለመፍጠርና ተጨማሪ የካፒታል አቅም ለከተማዋና ለሀገሪቱ ለመፍጠር እንዲቻል  በማሰብ የኢንቨስትመንት  መምሪያው ሊቋቋም ችሏል፤ ይህም በመሆኑ እና በተሰጠው ተጋባርና ሀላፊነት መሰረት በተሰራው ስራ  በእስካሁኑ ሂደት ከተማ አስተዳደሩ 845 ባለሃብቶች የኢንቨስትመንት ፈቃድ እንዲያወጡ እና ፈቃድ ካወጡት ውስጥ ደግሞ 102 ፕሮጀክቶች በአገልግሎት ዘርፍ እና በኢንዱስተሪው ዘርፍ በመሰማራት ወደ ስራ ገብተው ለ3500 ዜጎች የስራ ዕድል እንደፈጥር እና ለቀፃይም  የኢንቨስትመንት መምሪያው ያሉትን ሀብቶች ማለትም የኢንቨስትመንት አማራጮችና ምቹ ሁኔታዎች መረጃውን በመሰብሰብ፤አደራጂቶ   በመያዝና በማዘጋጀት የፕሮሞሽን ስራ በመስራት ተጨማሪ ባለሃብቶችን በመሳብና ለዜጎች የስራ ዕድል ለመፍጠርና ለከተማዋም ሀብት እንዲፈጥር ጥረት እያደረገ ይገኛል፡፡

 

Organizational Structure

ራዕይ

 የጎንደር ከተማ አስተዳደር በ2022 ዓ/ም በአምራች ኢንዱስትሪና በቱሪዝም በኢትዮጵያ ቀዳሚ ተወዳዳሪና ተመራጭየኢንቨስትመንት መዳረሻ ሆኖ ማየት ነው፡፡

ተልዕኮ

  • በአገር አቀፍ፣ ክልላዊና ከተማ አስተዳደራዊ ሁኔታዎች እና አዝማሚያዎች ጋር በማጣጣም የዘርፉን ማነቆዎች በመለየት እና የመፍትሄ አቅጣጫዎችን በማመላከት በክልሉ ለግሉ ክፍለ ኢኮኖሚ ሳቢ እና ምቹ ሁኔታዎች እንዲፈጠሩ ማድረግ፤ ተጨማሪ ለማንበብ

እሴቶች

  • የላቀ አገልግሎት፤
  • ዘመናዊነት፤
  • የተገልጋይ ርካታ፤ ዝግጁነት፤
  • ቅንጅታዊ አሰራር፤

ጠቃሚ መረጃ

አድራሻ