የኢንቨስትመንት ማስፋፊያ እና ኢንዱስ/ዞን ልማት

በኢንቨስትመንት ማስፋፊያ ኢንዱስትሪ ዞን ልማት ቡድን የሚሰጡ የዓገልግሎት አይነቶች 

የኢንቨስትመንት የማስፋፊ ሥራዎችን መስራት 

  • በጎንደርከተማ እና ዙሪያው ኢንቨስት ለማድረግ ያሉ ምቹ ሁኔታዎችንና የኢንቨስመንት አማራጮች በማስተዋወቂያ ስልቶች መያዝ እና ማስተዋወቅ፣ 
  • በዘርፉ የተሰማሩትን የኢንቨስትመንት ፕሮጀክቶች የሚገጥሟቸውን ችግሮችና መንስኤዎች ማጥናት፣ 
  • አዳዲስ የኢንቨስትመንት ፕሮጀክቶችን ወደ ዞኑ ለመሳብ  የኢንቨስትመንት ፕሮሞሽን መረጃዎች ተደራሽ ማድረግ፡፡ 
  • አዳዲስ የኢንቨስትመንት ፕሮጀክት ፕሮፋይሎችን ማዘጋጀት/እንዲዘጋጁ ማድረግና ትኩረት በተሰጣቸው የኢንቨስትመንት መስኮች ላይ ያነጣጠረ የኢንቨስትመንት ፕሮሞሽን በመስራት ኢንቨስትመንትን ማሳደግ/ማስፋፋት 
  • በራስ አቅም፤ በከፍተኛ ትምህርት ተቋማትና  አማካሪ የሚጠኑ የፕሮጀክት ሃሳቦችን ለይቶ ከሚመለከተው አካል ጋር በመተባበር እና እንዲጠኑ  በማድረግ የኢንቨስትመንት ፕሮሞሽን የአሠራር ሂደትና የገጽታ ግንባታ የሚሻሻልበትን ስልት እንዲቀየስ ያደርጋል፣ 
  • የባለሀብቶችንና የኢንቨስትመንት አስፈጻሚ አካላት የአቅም ግንባታ ስልጠናና ቅንጅታዊ አሰራር መፍጠር 
  • ባለሃብቶች ወደ ተለያዩ ኢንቨስትመንቶች እንደሰማሩ መሳብ፣ መደገፍና መከታተል፣ 
  • በኢንቨስትመንት ማስፋፋት ዙሪያ የአቅም ግንባታ ሥልጠና  መስጠት፣ 

የኢንቨስትመንት አዲስ፣ ትክ፣ ለውጥ ፈቃድ መስጠት፣ ማደስ፣ መሰረዝ፣ 

  • በኢንቨስትመንት ህጉ መሰረት የተሞላው ማመልከቻና አባሪ መረጃዎች ትክክል መሆናቸውን በማረጋገጥና ቅድመ-ሁኔታውን አሟልተው ሲገኙ ለሀገር ውስጥ ባለሃብቶች የኢንቨስትመንት ፈቃድ ይሰጣል፣ ያድሳል፣ ይተካል፣ ያሻሽላል፣ ያግዳል፣ ይሰርዛል፤   
  • ለመ/ቤቱ በተሰጠው ውክልና መሰረት የኢንቨስትመንት ፈቃድ ለተሰጣቸው ባለሃብቶች የንግድ ስራ ፈቃድ ጥያቄን መርምሮ የውሳኔ ሃሳብ ያቀርባል፣ቅድመ-ሁኔታውን አሟልተው ሲገኙ የንግድ ስራ ፈቃድ ይሰጣል፣ያድሳል፤ያግዳል፤ምትክ ይሰጣል፤ይሰርዛል፤ 
  • ለመ/ቤት በተሰጠው ውክልና መሰረት አዲስ ለሚመሰረቱ ድርጅቶች የመመስረቻ ፅሁፍና የመተዳደሪያ ደንብ ያዋውላል፣ 
  • በኢንቨስትመንት ፈቃድ አሰጣጥና በንግድ ስራ ፈቃድ አሰጣጥ ላይ አስፈላጊ የሆነውን ማብራሪያና ምክር ይሰጣል፣ 
  • በፈቃድ እድሳትና በንግድ ስራ ፈቃድ አሰጣጥና ሂደት የሚነሱ አቤቱታዎችንና ቅሬታዎችን በተመለከተ አግባብነት ካላቸውና ውክልና ከሰጡ መ/ቤቶች በቅርብ እየተገናኘ በመወያየት ለውሳኔ የሚያመች የመፍትሄ ሃሳቦችን አዘጋጅቶ ያቀርባል፣ 
  • የንግድ ማህበራት የስም ስያሜ አሰጣጥ ላይ የሚነሱ አቤቱታዎችን በተመለከ 
  • በንግድ ህጉ መሰረት መርምሮ የውሳኔ ሃሳብ ያቀርባል፣ 
  • ከውክልና ሰጭ መ/ቤቶችና ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በመነጋገር የዋና ንግድ ምዝገባ በሚቀርበው ጥያቄ መሰረት የሚከናወንበት ሁኔታ ያመቻቻል፣ 
  • ለሚሰጡ የፈቃድና የምዝገባ አገልግሎቶች አስፈላጊውን ክፍያ ያስፈጸማል፤ 
  • እንዲሰረዙ የተለዩ የኢንቨስተመንት ፈቃድ መረጃዎችን በየወቅቱ በመለየት ወቅታዊ ማድረግ /መሰረዝ/ 
  • ስለተከናወኑ የፈቃድና ምዝገባ አገልግሎቶች የተሟላና ወቅታዊ መረጃዎችን በሀርድና በሶፍት ኮፒ አደራጅቶ ይይዛል፣ ያሠራጫል ፤ 
  • መረጃዎችን በሀርድና በሶፍት ኮፒ አደራጅቶ መያዝና ለሚመለከተው አካል መስጠት፣ 
  • አዲስ የተሰጡ የኢንቨስትመንት ፈቃዶችን መረጃ በመጣራት ለዳታቤዝ ግብዓት ማዘጋጀት፣፣ 

የኢንዱስትሪ ዞን ልማት 

  • ዓለም አቀፍ ስታንዳርዱን ያሟላና ለልማት ዝግጁ የሆነ የኢንዱስትሪ ዞን ጥናት ማካሄድ፤ 
  • በክላስተር ለሚዘጋጁ  የኢንዱስትሪ ዞን የፕሮጀክት ፕሮፋይል ሰነድ ማዘጋጀት፤ 
  • የኢንዱስትሪ  ዞኖች ፕሮፋይል ሰነድ አዋጭነትን መገምገም ፤መከታተል፤ 
  • አልሚ ባለሃብቶችንና  አምራች ባለሃብቶችን ለመሳብ  የፕሮሞሽን ስራዎችን  መስራት፤ 
  • ለአልሚ ባለሃብቶች የተላለፈውን የማምረቻ ቦታ በትክክል ስራ ላይ መዋሉን መገምገምና የመከታተል ስራ መስራት፤ 
  • ፕሮጀክቶች መሰረተ ልማት( መንገድ፣ መብራት፣ ብድር፣ ውሃ) እንዲሟላላቸው ድጋፍ ማድረግ፣ 
  • ፕሮጀክቶች ከቀረጥ ነፃ ማበረታቻና የግብር እፎይታ እንዲያደኙ ድጋፍ ማድረግ፣ 
  • በውላቸው መሠረት የወሰዱትን መሬት ትግበራ ላይ ካላዋሉ አስፈላጊውን ክትትል በማድረግ በሬቱን ወደ መንግስት ተመላሽ እንዲሆንና እርምጃ እንዲወሰድባቸው የውሳኔ ሃሳብ ማቅረብና ተፈፃሚነቱን መከታል 
  • የኢንቨስትመንት ፕሮጀቶች ክትትልና ድጋፍ  መሬት እንዲያገኙ ለከንቲባ እና ለሚመለከተው አካል መላክ 
  • የፕሮጀክቶችን ፕሮፖዛል አዋጭነትን መገምገም እና መከታተል፤ 
  • ለኢንቨስትመንት ፕሮጀክቶች ክትትልና ድጋፍ በማካሄድ ወደ አፈፃፀም ማስገባት፣ 
  • የኢንቨስትመንት ፕሮጀክት መረጃዎችን መተንተን ፤ 
  • የአቅም ግንባታ እና የግንዛቤ ማስጨበጫ ሥልጠና  መስጠት፣ 
  • በመንግስት የተሰጡ የኢንቨስትመንት መብቶች በአግባቡ ስራ ላይ ስለመዋላቸው መከታተልና ማረጋገጥ፣ 

የኢንቨስትመንት ፕሮጀቶች ክትትልና ድጋፍ አገልግሎት መስጠት 

  • ውጤት-1፡- የስራ ድርሻዉን ማቀድ፤መፈፀም፤ማደራጀት እና ሪፖርት ማቅረብ 
  • ውጤት-2  የፕሮጀክቶችን ፕሮፖዛል አዋጭነትን መገምገም እና መከታተል፤ 
  • ውጤት-3፡-ለኢንቨስትመንት ፕሮጀክቶች ክትትልና ድጋፍ በማካሄድ ወደ አፈፃፀም ማስገባት፣ 
  • ውጤት 4 ፡ የኢንቨስትመንት ፕሮጀክት መረጃዎችን መተንተን ፤  
  • ውጤት 5፡ የአቅም ግንባታ እና የግንዛቤ ማስጨበጫ ሥልጠና  መስጠት፣ 
  • ውጤት 6 ፡በመንግስት የተሰጡ የኢንቨስትመንት መብቶች በአግባቡ ስራ ላይ ስለመዋላቸው መከታተልና ማረጋገጥ፣  
  • ፕሮጀክቶች ከቀረጥ ነፃ ማበረታቻ እንዲያደኙ ድጋፍ ማድረግ፣ 
  • ፕሮጀክቶች መሰረተ ልማት( መንገድ፣ መብራት፣ ብድር፣ ውሃ) እንዲሟላላቸው ድጋፍ ማድረግ፣ 
  • በውላቸው መሠረት የወሰዱትን መሬት ትግበራ ላይ ካላዋሉ አስፈላጊውን ክትትል በማድረግ በሬቱን ወደ መንግስት ተመላሽ እንዲሆንና እርምጃ እንዲወሰድባቸው የውሳኔ ሃሳብ ማቅረብና ተፈፃሚነቱን መከታል 

 

ኑ እና ጐንደርን እናልማ 

የጐንደር ከተማ አስተዳደር ኢንዱስትሪና ኢንቨስትመንት መምሪያ

ጠቃሚ መረጃ

አድራሻ